Announcements

የመግቢያ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ስለማሳወቅ
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ 4ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ፕሮግራም መስከረም 29 እና30/2017 ዓ.ም መሆኑ ቀደም ሲል ተገልጾ የነበረ ቢሆንም የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ባለመጠናቀቃቸው የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 14 እና 15/2017 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን።

READ MORE

 ለእንጅባራ ዩንቨርሲቲ አዲስና ነባር የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች በሙኑ፡-

  • 4ኛ ዓመት ተማሪዎች የመግብያ ጊዜ ከመስከረም 29-30/2017 ዓ.ም  
  • 3ኛ ዓመት ፤2ኛ አመት፤1ኛ አመት፤2017 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር አዲስ የተመደባችሁ እና በ2016 ዓ.ም ሬሚዲያል ትምህርት ወስዳችሁ ማለፍያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች መግብያ ጊዜ ጥቅምት 14-15/2017 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰብያ፡-

አዲስ ገቢ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ ብርድ ልብስ፤አንሶላ፤የትራስ ልብስ፤የስፖርት ትጥቅ፤8ኛ ክፍል ካርድ፤ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክብሪት እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም 3*4 የሆነ 4 ጉርድ ፎቶግራፍ መያዝ ይጠበቅባችኃ፡፡

እንጅባራ ዩንቨርሲቲ

READ MOR

ለኤክስቴንሽን ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በቅዳሜና እሁድ (Weekend Extension) መርሃ-ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ አዲስ አመልካቾችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ከመስከረም 08 እስከ 18 / 2017 ዓ.ም ባሉት ቀናት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ዩኒቨርሲቲው የሚሰጣቸው የስልጠና መስኮች እና የመግቢያ መስፈርቶች ዝርዝር እንደሚከተለው ተገልጸዋል፡፡

READ MOR


READ MOR