የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የ2016 በጀት ዓመት የአስተዳደር ዘርፍ ዓመታዊ የሥራ አፈፃጸም ግምገማ አካሄደ

ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርቱ በአስተዳደር እና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ስር ባሉ እንዲሁም የአካዳሚክ ዘርፍ አስተዳደራዊ ስራ ክፍሎች የአፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በግምገማው የተገኙት የእንጅባራ አስተዳደር እና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዝዳንት ወሀቤ ብርሃን(ዶ/ር) ግምገማው በ2016  በጀት አመት የተከናወኑ ተግባራትን አፈጻጸም በማየት መልካም ተሞክሮችን እና ስኬቶችን ለማስቀጠል እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮችን በ2017 ዓ.ም  በጀት ዓመት ለማስተካል የተካሄደ መሆኑን ተናገረዋል፡፡

አያይዘውም በ2016 በጀት ዓመት በተለይም በግዥ እና ዕቃ አቅርቦት ላይ ችግሮች ቢኖሩም ይህን ችግር በመቋቋም ዓመቱን በስኬት ያጠናቀቅንበት በጀት ዓመት ነውም ብለዋል፡፡
ባለው ወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት ለአካዳሚክ ዘርፉ የሚያስፈልጉ ላፕቶፕ፣ የጽህፈት መሳሪያዎችን የመሳሰሉ ቋሚ እና አላቂ እቃዎችን በወቅቱ ለማቅረብ ችግር የነበረበት ዓመት መሆኑን አስታውሰው ለቀጣይ በጀት ዓመት ችግሮችን ለመቅረፍ በሚያስችል መልኩ  የመፍትሄ አቅጣጫዎች መቀመጣቸውን ተናግረዋል፡፡

ግምገማው ለሁለት ቀናት የተካሄደ ሲሆን በአስተዳደር እና ልማት ም/ፕሬዝደንት ሥር ካሉ ስራ ክፍሎች በተጨማሪ የቤተ መጽሐፍት እና የሬጅስትራር ሥራ አስፈጻሚ ክፍሎችም ዓመታዊ ሪፖርት አቅርበው ግምገማ ተደርጓል፡፡

ሐምሌ 23/2016 ዓ፣ም፤እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ