እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከአየሁ ጓጉሳ ወረዳ ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚሆን የቆርቆሮ ድጋፍ አደረገ

ዩኒቨርሲቲው በወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት ከአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር አየሁ ጓጉሳ ወረዳ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ የሚሆን ከ1ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ከ1ሽህ 5መቶ በላይ ዚንጎ ቆርቆሮ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ክንዴ ብርሃን(ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው ለማህበረሰቡ በርካታ ድጋፎችን ሲያደርግ የቆየ መሆኑን ገልጸው በዛሬው ዕለት በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር አየሁ ጓጉሳ ወረዳ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች የቤት ክዳን የሚሆን ከ 1ሚሊዬን ብር በላይ ግምት ያለው 1,516 ዚንጎ ቆርቆሮ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የአየሁ ጓጉሳ ወረዳ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ባለሙያ የሆኑት አቶ ቦጋለ ቢሻው በበኩላቸው በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት በወረዳው አምበላ እና ጎሬ አካባቢዎች በርካታ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውንና መውደማቸውን ገልጸው ዩኒቨርሲቲው ይህን ችግር ለመቅረፍ ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ሐምሌ 26/2016ዓ.ም

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ