በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ተካሄደ

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች እና የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብሩ ላይ ተሳትፋዋል፡፡

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ እንደ ሀገር ትኩረት ለተሰጠው አረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የራሱን ሚና እየተወጣ የሚገኝ ሲሆን በተለይም ባለፈው ዓመት ከአንድ መቶ ሺ በላይ ችግኝ መተከሉን የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝደንት ክንዴ ብርሃን (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡ በዛሬው እለትም የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ እና የከተማው ወጣቶች በጋራ በመተባበር ከ20 ሺ በላይ ችግኝ በሊዊ ተራራ ላይ መተከላቸውን ገልጸዋል፡፡

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ እና በቻግኒ ችግኝ ጣቢያ የሚያፈላውን ችግኝ በራሱ ግቢ ከመትከሉም በላይ ለማህበረሰቡ በተለይም ለተደራጁ ተቋማት በተመጣጣኝ ዋጋ እና በስጦታ ወስደው እንዲያለሙ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡ አያይዘውም ዩኒቨርሲቲው በውበት ችግኝ ብቻ ከማልማት በተጨማሪም በግቢው ውስጥ እንደ አፕል ያሉ ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞችን መተከላቸውን አብራርተዋል፡፡

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ

ሐምሌ 30/2016 ዓ.ም