በስርዓተ ትምህርት ዝግጅት እና ትምህርት ምዘና ላይ ያተኮረ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጠ

ለእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህራን በስርዓተ-ትምህርት ዝግጅት እና በትምህርት ምዘና ላይ ያተኮረ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሠጥቷል፡፡

ስልጠናውን የከፈተቱት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ እና ማጎልበቻ ኦዲቲንግ ስራ አስፈጻሚ ዓለም አምሳሉ( ዶ/ር) የስልጠናው ዓላማ መምህራን በትምህርት ምዘና እና በመማሪያ ግብዓቶች ዝግጅት ዙሪያ የተሻለ ግንዛቤን እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

ስልጠናውን የሰጡት የዩኒቨርሲቲው የመምህራን ትምህርትና ስርዓተ ትምህርት ጥናት ትምህርት ክፍል መምህርና የከፍተኛ ዲፕሎማ ስልጠና አስተባበሪ የሆኑት ቱጂ ኢሬሶ(ረዳት ፕሮፌሰር) እና የሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት ሙሉዓለም አለማየሁ ናቸው፡፡

ስልጠናው በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከትምህርት ጥራት ማረጋገጫ እና ማጎልበቻ ኦዲንቲንግ ስራ አስፈጻሚ በጋራ የተዘጋጀ ሲሆን ለሁለት ቀናት ሲሰጥ ቆይቶ በዛሬው እለት ተጠናቋል፡፡

መስከረም 21/2017 ዓ.ም

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ