ለእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ህክምና መጽሃፍት እና ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደረገ

ለእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ህክምና መጽሃፍት እና ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደረገ።
ዩኒቨርሲቲው ከቅዱስ ፓውሎስ፣ ጥቁር አንበሳ እና የካቲት 12 ሆስፒታሎች ከ1 ሚሊዮን ብር ባለይ ግምት ያላቸው መጽሃፍት እና ቁሳቁሶች ድጋፍ ማግኘቱ ተገልጿል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ትምህር ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ቃለዓብ እሱባለው ድጋፉ የተገኘው ከቅዱስ ፓውሎስ፣ጥቁር አንበሳ እና የካቲት 12 ሆስፒታሎች መሆኑን ገልጸው 380 የሚሆኑ የህክምና መፅሃፍት ፣መድሃኒቶች እና ቁሳቁሶች ሲሆኑ ግምታቸው ከ1 ሚሊዮን 500 ሽ ህ ብር በላይ መሆናቸውንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ዶ/ር ቃለዓብ አክለውም ሆስፒታሎቹ ከዚህ በፊትም የተለያዩ ድጋፎች ማድረጋቸውን ገልጸው ለተደረገው ድጋፍም ምስጋናቸውን አቅርበው በደጋፍ የተረከቡትን መጽሃፍትንም ለዩኒቨርሲቲው ቤተ-መጽሃፍት ገቢ አድርገዋል፡፡
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በሀገራችን የተሻለ ህክምና ከሚሰጥባቸው ግንባር ቀደም የህክምና ተቋማት ድጋፍ በመደረጉ ከልብ የመነጨ ምስጋናውን እያቀረበ የጤናውን ዘርፍ ለማሻሻል በትኩረት እንደሚሰራም ተገልጿል፡፡

ነሐሴ 9/2016 ዓ.ም

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ